ወግ

 አዝናኝ ቀል 
     አስተማሪዋ ክፍል ውስጥ እያስተማረች ነው፡፡በመሃል ትንሹ ቤቢ አትኩሮቱ ትምህርቱ ላይ እንዳልሆነ ስላየች የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቀችው
   ቲቸር፡- “3 እርግቦች አጥር ላይ ብታይና አንዷን በጥይት ብትመታት ስንት ወፎች ናቸው አጥሩ ላይ የሚቀሩት?”
   ትንሹ ቤቢ፡- “ምንም አይቀርም፡፡”
   ቲቸር፡- “ለምን?”   ትንሹ ቤቢ፡- “ምክንያቱም የጥይቱ ድምፅ ሁሉንም ስለሚያስደነግጣቸው ሁሉም አይኖሩም፡፡”
  ቲቸር፡- “አይ እንደሱ አይደለም፡፡ መልሱ 2 ነው እሺ፡፡ ግን አስተሳሰብህን ወድጄልሃለሁ፡፡”
         በዚህ ጊዜ ትንሹ ቤቢ በጣም ተናደደ፡፡ ስለሆነም በተራው ይን ጠየቀ፡፡
ትንሹ ቤቢ፡- “እሺ 3 ሴቶች ከአይስክሬም መሸጫ ሱቅ አይስክሬም ገዝተው ወጡ እንበል፡፡ ከዛ አንደኛዋ አይስክሬሙን በቅብጠት ትልሰዋለች፣ አንደኛዋ ደግሞ በእርጋታ አይስክሬሙን ትመጠዋለች፣ ሦስተኛዋ ደግሞ አይስክሬሙን በችኮላ ትነክሰዋለች፡፡ እና ከሦስቱ መካከል ትዳር ያላት የትኛዋ ናት?”ቲቸር፡- “አይስክሬሙን በእርጋታ የምትመጠው ናታ፡፡”
ትንሹ ቤቢ፡- ፈገግ ብሎ “ተሳስተሻል፡፡”
ቲቸር፡- “ለምን?”ትንሺ ቤቢ፡- “ምክንያቱም ከሦስቱ መካከል ትዳር ያላት በእርጋታ አይስክሬም የምትመጠው ሳትሆን እጇ ላይ የትዳር
ቀለበት ያረገችው ናት እሺ፡፡ በነገራችን ላይ አስተሳሰብሽን ግን ወድጄልሻለሁ፡፡”

                                    አዝናኝ ቀል 


ልጁ የቆመ አሮፒላን ያይና ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ ሮጦ ገባና. . .
የአሮፒላኑ ኮክፒት
(ጋቢና) ውስጥ
"አሮፒላንን የማብረር ጥበብ"የሚል መፅሀፍ አየ ሲገልጠው. . .
ገፅ
_1_ "ሞተር ለማስነሳት ቀዩን ይጫኑ" ይላል ለምን አልሞክረውም አለና ተጫነው!
ሞተሩ ተነሳ
. . .ገፅ_2_ "ወደፊት ለማንደርደር ቢጫውን ይጫኑ"ይላል ተጫነው! አሮፒላኑ በፍጥነት ተንደረደረ. . .ገፅ_3_ "ወደ አየር ለማስነሳት ሰማያዊውን ይጫኑ"ይላል ተጫነው አሮፒላኑ አየር ላይ መብረር ጀመረ በጣም ተደስቶ አስር ደቂቃ ያህል ከበረረ ቦሃላ"ይበቃኛል ላሳርፈው"ብሎ
ሲገልፀው. . .ገፅ_4_ "ለማሳረፍ ቁጥሩ 2 መፅሀፍ ገዝተው ያንብቡ


አዝናኝ ቀልዶችና አባባሎች
አባት: ከኔ እና ከእናትህ የምትወደው ማንን ነው ?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: የበለጠ እምትውደው ?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: አንተ አንዱን ተናገር ?
ልጅ: ሁለታችሁንም
አባት: እሺ እኔ ባህርዳር ብሄድ እናት ደግሞ ሀዋሳ ብትሄድ ወዴት ትሄድ ነበር ?
ልጅ: ሀዋሳ
አባት: አሀ... እናትህን ነው የበለጠ የምትወደው ማለት ነው
ልጅ: አደለም ሀዋሳ ስለምትመቸኝ ነው
አባት: እሺ እኔ ሀዋሳ ብሄድ እናትህ ደግሞ ባህርዳር ብትመጣ የት ትሄድ ነበር ?
ልጅ: ባህርዳር
አባት: በቁጣ ለምን ?
ልጅ: ሀዋሳ ሄጄ ነበራ


                         

      አይ ቀልድ

አንድ ሱቅ 90% ዲስካውንት እንዳደረገ በተለያዩ ማስታወቂያዎች ላይ ያነበበው የከተማው ነዋሪ ሱቁ በር ላይ ወረፋ መያዝ የጀመረው ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ነው ::ጠዋት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በር ላይ ሰልፍ ይዘው በሚጠባበቁበት ግዜ አንድ ደቃቃ ሰውዬ በሰልፈኞቹ መሀል እየተጋፋ ከሰልፉ ፊት ወዳሉት ሰዎች እንደደረሰ "ሂድ ወረፋህን ጠብቅ " ብለው ገፈታትረው ወደ ውሀላ ይወረውሩታል ::እንደምንም ሚዛኑን ጠብቆ በድጋሚ ወደፊት ገስግሶ ሲመጣ "ሰውዬ ወረፋህን ጠብቅ ስትባል አትሰማም ?" ብለው በቦክስ እየተቀባበሉ ያላጉታል :: መሬት ወድቆ ትንሽ ከተንፈራፈረ ቦሀላ እንደምንም ብሎ ይነሳና በምሬት ይህን ተናገረ ::"ወላሂ ..... ከዚህ በውሀላ አንድ ሰው ንክች ቢያደርገኝ እችን ሱቅ አልከፍታትም

                                  ደስ የሚል ቀልድ ሰማሁ ......    

የሆኑ ቻይናዎች ንፋስ ስልክ በሚገኘው በዬሴፍ የመቃብር ስፍራ ያልፋሉ:: የመቃብሩን ስፋር ትልቅነት ከተመለከቱ በኋላ "ይህንን የሚያክል ቦታ ምነው ዝም ብላችሁ አስቀመጣችሁት ለምን ለኢንቬስተር አትሰጡትም" ብለው ይጠይቃሉ አብሯቸው ያለውን አበሻ:: አበሻውም መልሶ "አይ ይህ እኮ የመቃብር ስፍራ ነው" ይላቸዋል:: ቻይናዎቹም "እንዴ ለምን ትቀብራላችሁ ማቃጠል ነው እንጂ" ይላሉ:: አበሻው መልሱ "እኛ ሀገር በቁም ነው የምናቃጥለው አለ" አሉ::

 

Top 20 Most Visited Websites in The World Right Now based on linking Root Domains 

RankRoot DomainLinking Root DomainsExternal Links
1Facebook.com9,648,8202,147,483,647
2Twitter.com6,395,8582,147,483,647
3Google.com6,342,7131,144,724,201
4Youtube.com5,070,955887,260,910
5WordPress.org3,970,817510,039,817
6Adobe.com3,958,006356,388,940
7Blogspot.com3,409,5461,235,499,979
8Wikipedia.org2,956,500267,843,744
9Godaddy.com2,875,7161,202,140,160
10WordPress.com2,309,424730,002,485
11Yahoo.com2,199,360307,307,946
12Linkedin.com1,971,296370,486,778
13Amazon.com1,532,919390,152,610
14W3.org1,460,259382,346,008
15Flickr.com1,404,713396,827,562
16Apple.com1,272,623133,783,011
17Myspace.com1,254,181163,041,672
18Outright.com1,190,94419,897,239
19Digg.com1,097,766210,005,478
20Tumblr.com1,027,056164,635,65